220
likes
29
comments
daily view 0
monthly view 0
Live Analytics
Comments 0
⏩ግንቦት 14 🙏➕ እንኳን ለብፀዕ አቡነ አረጋዊ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳቹ❗🙏➕የተመረጡ የአቡነ አረጋዊ መዝሙሮችን ያድምጡ #abune aregawi Analytics Table
Income Estimates for ⏩ግንቦት 14 🙏➕ እንኳን ለብፀዕ አቡነ አረጋዊ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳቹ❗🙏➕የተመረጡ የአቡነ አረጋዊ መዝሙሮችን ያድምጡ #abune aregawi
Based on this YouTube video's total view count of 4.00K views and industry-standard rates, the estimated total earning is $3 - $8 through ad revenue. Historical data is not yet available to calculate daily, weekly, or monthly averages.
About ⏩ግንቦት 14 🙏➕ እንኳን ለብፀዕ አቡነ አረጋዊ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳቹ❗🙏➕የተመረጡ የአቡነ አረጋዊ መዝሙሮችን ያድምጡ #abune aregawi
Explore ⏩ግንቦት 14 🙏➕ እንኳን ለብፀዕ አቡነ አረጋዊ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳቹ❗🙏➕የተመረጡ የአቡነ አረጋዊ መዝሙሮችን ያድምጡ #abune aregawi with 4,001 views, 220 likes, and 29 comments. Experience the impact of this video content that has captured audience attention.
ግንቦት 14 እንካን ለጻድቁ አቡነ አረጋዊ አመታዊ ክብረ በአል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ ጻድቁ አቡነ አረጋዊ እኚህ አባት ከተሰሐቱ ቅዱሳን (ከሮምና ኤሽያ ከመጡት ከ9 ቅዱሳን አባቶች አንዱ ሲሆኑ አባታቸው ይስሐቅ የሮም ንጉስ ነበር፡፡ እናታቸው ንገሰተ እደና ትባላለች፡፡ የመጀመሪያ ስማቸው ዘሚካኤል ነው፡፡ ጥበብ መንፈሳዊ ሲማሩ አድገው ወደ እሰከነድረያ ኮብልለው ገዳም ገቡ፡፡ አበምኔቱ አባ ጳኩሚስ በፈቃደ እግዚአብሔር የመጡ መሆናቸውነ አውቀው መዓርገ ምንኩስና ሰጥተዋቸዋል፡፡ ንጉስ የሆኑ ቤታቸው የሞቀ ቤተ ሰቦቻቸውነ ንቀው ትተው ገዳም ገብተው በምንኩስና ተወስነዋል፡፡ አበምኔቱም ወደዚህች የሕየወት መንገድ ስለመራሀን ብፁህ አረጋዊ መባል ይገባሃልብለዋቸዋል፡፡ አረጋዊ የተባሉት ከዚያ ወዲህ ነው፡፡ አባታችን በተጋድሏቸውም ከአባ እንጦንስ፣ ከአባ ጳውሊ እና ከአባ መቃርስ ቀጥሎ በአራተኛ መዐረግ አበ መነኮሳት ሆነው ተመርጠዋል። በገዳመ ዳውናስ 7 ዓመት ከቆዩ በኋላ ወደ ሮም ተመልሶ ሲያስተምሩየሀገራችንን ዜና ሰምተው ለመምጣት በ480 ዓ.ም ከአባ ፍሪሚናጦስ ቦ|ላ መንገድ ጀመሩ፡፡ ቅዱስ ሚካኤል በክነፉ ተሸክሞ አክሱ አድርሷቸዋል፡፡ ተመልሶ ሄደው ስለ ኢትዮጵያ ቅድስት ሀገር መስክረዋል፡፡ ሐዋርያ ሳይላክላት በሃይማኖት በምግባር ጸንታ ትኖራለች ብለው ለሰባቱ ዘመዶቻቸው አበውመነኮሳት ነገሯቸው፡፡ ስምንቱ ሁሉ ጓዛቸውን ጠቅልለው በሮም ነግሶ የነበሩ ይስሐቅን (አባ ገሪማን) ጨምረው ንጉስ አልአሜዳ በነገሰ በአምስተኛ ዓመት ማለትም በ480 ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ ራሳቸውን ዘጠኝ ሆነው መጥተዋል፡፡ አባ አረጋዊ እናታቸው ቅድስት እድናን ደቀመዝሙራቸውን ማትያስን አስከትለው እግረመንገዳቸውን እያስተማሩና ድውያንን እየፈወሱ ደብረ ዳሞ ደረሱ፡፡ ከእግረ ደብር ሆነው አሁን ይህን ተራራ በምን ልወጣው እችላለሁ እያሉ ሲያወጡ ሲያወርዱ በንግግሩ ሐሰት የሌለበት አምላካችን በነቢዩ ዳዊት ላይ አድሮ በመዝሙር 90/91፡11-16 ላይ “በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዛቸዋልና፤ እግርህም በድንጋይ እንዳትሰናከል በእጆቻቸው ያነሡሃል። በተኵላና በእባብ ላይ ትጫማለህ፤ አንበሳውንና ዘንዶውን ትረግጣለህ። እንዳለው የታዘዘ ዘንዶ መጥቶ ስደሳ ክንድ በሚያህል ጅራቱ ጠምጥሞ ቅዱስ ሚካኤል ሰይፈ እሳት ይዞ እየጠበቃቸው ከተራራው አናት አድርሷቸዋል፡፡ ወዲያው ሃሌ ሉያ ለአብ ሃሌ ሉያ ለወልድ ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ ብለው አመስግነዋል፡፡ ቦታውም ደብረ ሃሌ ሉያ ተብሏል፡፡ በዚያ ዕለት ግማሽ ህብስት በልተው ጠገቡ፤ ከዚያ በኋላ ግን ምድራዊ ሕብስት አልተመገቡም፡፡ በሰንበተ ክርስታያን ከቅዳሴ በኋላ ሕብስተ ሰማያዊ እያመጡላች ይመገቡ ነበር እንጂ፡፡ ኋላ ግን ዜና ጽድቃቸውን ሰምተው ከስድስት ሺህ ያላነሱ ደቀ መዛሙርት ተሰብስበውላቸዋል፡፡ ዘጠና ዘጠኝ አመት ሲሞላቸው ጌታ በመንፈቀ ለሊት ተገልጾ ምድራዊ መንግስትህን ትተህ ስላገለገልከኝ ህልፈት ሽረት የሌለባት ሰማያዊ መንግስቴን አወርሰሃለሁብሎ ቃልኪዳን ሰጣቸው፡፡ በስምህ የተማጸነውን እስከ አስራ አምስት ትውልድ ድረስ እምርልሃለሁ አንተም ከሞት ገጽ ትሰወራለህ ብሎ ተስፋቸውን ነገራቸው፡፡ እሳቸው መነኮሳቱን ሰብስበው ከእንግዲህ በሥጋ አታዩኝም ብለው ነግረዋቸው አበምኔት (የገዳም አባት ወይም አለቃ) ሾመውላቸው ጥቅምት አሥራ አራት ቀን በዚያው በደብረ ዳሞ ተራራ በስተምስራቅ አቅጣጫ እንደሄኖክ እንደ ኤልያስ ተሰውሯል፡፡ በረከታቸው፣ ቃልኪዳናቸው፣ አማላጅነታቸው በሁላችን ይደር አሜን። #abune aregawi በዓለ ልደቱ ለአቡነ አረጋዊ ጥር ፲፫ ቀን ፳፻፲፬ ዓ.ም የጻድቁ የአቡነ አረጋዊ አባት ይስሐቅ እናቱም እድና ይባላሉ፡፡ ሁለቱም እግዚአብሔርን የሚፈሩና የሚያከብሩ ነበሩ፡፡ እግዚአብሔር አምላክም የተባረከውን ልጅ ሰጣቸው፤ይህም የሆነው በጥር ፲፬ ቀን ነው፡፡ እግዚአብሔርን መፍራት፣ ሕገ ኦሪትን ትምህርተ ነቢያትንና ቅዱሳት መፃሕፍትን እያስተማሩ አሳደጉት፡፡ እርሱም በመንፈስ ቅዱስ ኃይል እየጸና እየበረታ አደገ፡፡ ሚስት ያገባ ዘንድ አጩለት፡፡ ጻድቁ አባታችን አቡነ ዘሚካኤል(አረጋዊ) ፈጽሞ እምቢ አለ፡፡ ከብዙ ዘመን በኋላ ከሮም ወደ ግሪክ ሀገር አባ ጳኩሚስ የሚኖርበት ደውናስ ወደምትባል ገዳም የምንኩስናን ልብስ ይለብስ ዘንድ ሄደ፡፡ አባ ጳኩሚስንም አገኘው፡፡ አባ ጳኩሚስም ‹‹ልጄ ሆይ፥ አንተ የንጉሥ ልጅ እንደ መሆንህ መጠን የመንግሥቱ ወራሽ ነህና መንኰሰህ ለመኖር ይቻልሃልን?›› አለው፡፡ ብፁዕ አባታችንም ‹‹አባቴ ሆይ፥ የምድር መንግሥት ኃላፊ ጠፊ ነው፤ ነገር ግን የማታልፈውን የማትጠፋውን ዘለዓለማዊት መንግሥት እወርስ ዘንድ እፈልጋለሁ›› አለው፡፡ በፈተናም ከጸና በኋላ በዐሥራ ዐራት ዓመቱ በአባ ጳኩሚስ እጅ የምንኩስናውን ልብስ ለበሰ፡፡ ከአመነኮሰውም በኋላ ስሙን ዘሚካኤል ብሎ ሰየመው፡፡ ከአባ እንጦንስ ዐራተኛው የቆብ ልጅ ሲሆን እርሱን በቆብ የሚወልደው ደገኛውን የገዳም ሥርዓትን ከሠሩልን አበው አንዱ የሆነው ታላቁ ቅዱስ ጳኲሚስ ነው። ቀድሞም በአባ ጳኲሚስ ዘንድ መንኲሶ ለመኖር ሲመጣ የመጣው ከንጉሥ ቤት ነበርና አባ ጳኲሚስ ከማመንኰሱ በፊት ብዙ ፈትኖታል። በኋላም ገና ልጅ ሳለ በዐሥራ ዐራት ዓመቱ አመነኰሰው። የምንኲስና ስሙንም አባ ዘሚካኤል ብሎ ሰየመው። አረጋዊ የተባለው ገና ወጣ ሁኖ ሳለ ልባዌውና ግብሩ ሁሉ እንደሚያስተውል አረጋዊ ነውና ‹‹አንተስ አባታችን አረጋዊ ነህ›› ብለው ጠሩት። በገድልም ተጸምዶ የሚኖር ሆነ። በኋላም ከሁለት ደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ከተመለከታት በኋላ ወደ ሮም ተመልሶ ለወንድሞቹ ለስምንቱ ቅዱሳን ነገራቸውና እየመራ አብረው መጥተው በኢትዮጵያ መኖር ጀመሩ። በኋላ እነርሱ በአንድነት መኖራቸው ለወንጌልና ለምንኲስና መስፋት አይሆንም ነበርና ሀገሪቱን ተከፋፈሏት። በዚህም አባታችን አቡነ አረጋዊ ወደ ትግራይ በተለይም ወደ ደብረ ዳሞ መጦና በዚያ በዓታቸው ወሰኑ። በእሊህ ዘጠኝ ቅዱሳን ወደ ኢትዮጵያ መምጣት እጅግ ብዙ የሐዋርያዊ አገልግሎት እንዲሰፋ ሆኗል። አባ አረጋዊም ወደ ደብረ ዳሞ ለመውጣት በአደዱ ጊዜ የታዘዘ ዘንዶ ከወገባቸው ይዞ አውጥቷቸዋል። በዚያም ሲጋደሉ ከኖሩ በኋላ ያማረች ቤተ ክርስቲያንን ሠሩና መወጣጫውን ‹‹ዳህምሞ-አፍርሰው›› ብለው አስፈረሱት። በዚህም ዳሞ ተብላ እንደተጠራች ይነገራል። እርሳቸውም በገድል ተጸምደው ከኖሩ በኋላ በዚያችው ገዳማቸው ሳሉ ወደ ብሔረ ሕያዋን ተሠውረው ሄደዋል። እኒህ ደግ ጻድቅ ከቅዱስ ያሬድም ጋር የሚነገርላቸው ግሩም ዜና አላቸው። የጻድቁ በረከት በሁላችንም ይደርብን። እግዚአብሔርም በጸሎታቸው ይማረን፤ ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፥ ስንክሣር ዘወርኃ ጥቅምት፣ ገድለ አቡነ አረጋዊ
About YouTube Real-Time View Count
With SocialCounts.org’s view counter, track your YouTube video’s live view count and YouTube likes count in real time with fast, reliable updates.
Watch every YouTube video live view count rise with our real-time YouTube views tracker—built for accuracy and minimal delay.
Follow YouTube real time views as they happen, using our dedicated view counter for YouTube videos.
Get up-to-date live view count on YouTube and see real-time growth with SocialCounts.org’s smart tracking tools.
Embed Widget
Parameters:
fullscreen=true- Fullscreen countergraph=true- Live graph chartcounter=0/1/2- Select counter (0=likes, 1=views, 2=comments)
URL
Click to copy the embed URL to your clipboard

